በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተመድን በመቃወም የወጡ 48 ሰዎች ተገደሉ


ፋይል - የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በመቃወም በጁባ የተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ - መጋቢት 10፣ 2014
ፋይል - የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በመቃወም በጁባ የተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ - መጋቢት 10፣ 2014

በምሥራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በመቃወም በወጡ ሰልፈኞች ላይ በተወሰደ ርምጃ፣ ቢያንስ 48 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ምንጮች እና ኦፊሴላዊ ሰነዶች ጠቁመዋል።

ትናንት ረቡዕ፤ የኮንጎ ወታደሮች፣ የአንድ ሐይማኖት ተከታዮች በሀገሪቱ የሚገኘውን የመንግስታቱን ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይል በመቃወም ሰልፍ ሊያደርጉ ሲሞክሩ አስቁመዋቸዋል።

ወታደሮች ወደ አንድ ራዲዮ ጣቢያ እና የሐይማኖት ተቋም ሲገቡ፣ 10 ሰዎች ተገድለው እንደነበር ቀድመው የወጡ መረጃዎች ጠቁመው ነበር። በሁከቱ አንድ የፖሊስ አባል በስቅላት ተገድሏል ተብሏል።

የኤኤፍፒ ዜና ወኪል የተመለከተውና፣ የጸጥታ ባለሥልጣናት ያረጋገጡት የሠራዊቱ የውስጥ ሰነድ እንዳመለከተው፣ የፖሊስ አባሉን ጨምሮ 48 ሰዎች ሲገደሉ፣ 75 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ወታደሮች የሐይማኖት ቡድን መሪውን ጨምሮ 168 የሚሆኑ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ሲያደርጉ፣ ስለት ያላቸው መሣሪያዎችንም ይዘዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወሩ ያልተረጋገጡ ምስሎች፣ ወታደሮች በደም የተሸፈኑ አስከሬኖችን ወደ መኪና ላይ ሲወረወሩ አሳይተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG