በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል ቡርሃን ጦርነቱን በአስቸኳይ ማቆም እንደሚሹ በግብጽ ጉብኝታቸው ገለጹ


አል ቡርሃን ጦርነቱን በአስቸኳይ ማቆም እንደሚሹ በግብጽ ጉብኝታቸው ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:57 0:00

የሱዳን ጦር ሠራዊት አዛዥ እና አገሪቱን በኦፊሴል የሚያስተዳድረው ጊዜያዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ጀነራል አብደል ፋታሕ አል-ቡርሃን፣ ከትላንት በስቲያ ሰኞ፣ በግብጽ የባሕር ዳርቻ በምትገኘው የኤል አላሚን ከተማ፣ ከአገሪቱ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታሕ አል-ሲሲ ጋራ ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

የአል-ቡርሃን የግብጽ ጉብኝት፣ ጦርነቱ በሱዳን ከተጀመረበት ካለፈው ሚያዝያ ወር ወዲህ፣ የመጀመሪያው የውጪ ሀገር ጉብኝት ነው፤ ተብሏል፡፡

ጀነራሉ፣ በግብጹ አል-ሲሲ፣ ለአንድ ሀገር መሪ የሚደረግ የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ ሠራዊታቸው፣ ለብቻው ሥልጣንን የመቆጣጣር ፍላጎት እንደሌለው የገለጹት አል ቡርሃን ተናግረዋል። ዋናው ግባቸውም፣ ለአራት ወራት የቆየውን ጦርነት በአስቸኳይ ማቆም እንደኾነ አክለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ።

XS
SM
MD
LG