በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ተመርዟል ከተባለው ባህር የወጣ ምግብ ሲመገቡ አሳዩ


ፋይል - ፋኩሺማ በሚገኘው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሚገኙት እና ራዲዮ አክቲቭ ቆሻሻ ውሃ ይዘዋል የተባሉት ውሃ ማጠራቀሚያዎች ሐምሌ 14፣ 2023
ፋይል - ፋኩሺማ በሚገኘው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሚገኙት እና ራዲዮ አክቲቭ ቆሻሻ ውሃ ይዘዋል የተባሉት ውሃ ማጠራቀሚያዎች ሐምሌ 14፣ 2023

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ፣ ከጃፓን የኒውክለር ጣቢያ ወደ ባህር ተለቋል የተባለውን የሬዲዮ አክቲቭ ተከትሎ ሁሉም የጃፓን ባህር ምግቦች ወደ አገሯ እንዳይገቡ ቻይና የጣለችውን እገዳ ለማስተባበልና እገዳው የተጣለባቸውን የአካባቢ ነዋሪች ለመደገፍ ዛሬ ረቡዕ በጽ/ቤታቸው የሳሺሚ ምሳ ግብዣ ማድረጋቸው ተነገረ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚኒስትሮቻቸውን በመጋበዝ ከፋኩሺማ ግዛት የተገኙ የሳሺሚ የባህር ምግቦችን ሲመገቡ በቴሌቪዥን አሳይተዋል፡፡

የጃፓን ኢኮኖሚ ፣ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ያሱቶሺ ኒሺሙራን ጨምሮ የፋይናንስ ሚኒስትሩና ሌሎች ባለሥልጣናት በምሳ ግብዣው መገኘታቸው ተዘግቧል፡፡

ቻይና በጃፓን የባህር ምግቦች ላይ እገዳውን የጣለችው ፋኩሺማ ዳይቺ በሚገኘው የኒውክለር የኃይል ማመንጫ ላይ እኤአ በ2011 ከደረሰው ከፍተኛ የተፈጥሮ ጉዳት በኋላ፣ ጃፓን ካላፈው ሳምንት ሐሙስ እኤአ ከነሀሴ 24 ጀምሮ የአካባቢውን ውሃ ቀስ በቀስ መልቀቅ በመጀመሯ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በኒውክሌር ተቋሙ አካባቢ በተደረገው ምርመራ ምንም ዓይነት የራዲዮ አክቲቭ ንጥረ ነገር አለመገኘቱንና የውሃው ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን ጃፓን አስታውቃለች፡፡

በጃፓኑ ተቋም የደረሰው አደጋ፣ ከዛሬ 25 ዓመት በፊት በቸርኖቢል ከደረሰው አደጋ ወዲህ፣ በኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ተቋም ላይ የደረሰ ከፍተኛ አደጋ መሆኑ ተነግሯል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG