በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም መሪዎች እና ዕድሜያቸው


የዓለም መሪዎች እና ዕድሜያቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:12 0:00

በአሁኑ ጊዜ ዓለማችን፣ የዕድሜ ባለጸጎች በብዛት ያሉባት ዓለም ናት፡፡ በንጽጽር፣ ከቀድሞው ይልቅ ዛሬ፣ ሰዎች ለረጅም ጊዜ በሕይወት ይኖራሉ፡፡ መኖርም ብቻ አይደለም፤ በሽምግልና ዘመናቸው ብዙ ሥራ ያከናውናሉ፡፡

በተለመደው የጡረታ ዕድሜ፣ “በቃኝ” ብለው ሳይሰናበቱ፣ በተመረጡበት የሓላፊነት ቦታ ሥራቸውን የሚቀጥሉ የፖለቲካ ሰዎችም ዐያሌ ናቸው፡፡ በአኹኑ ወቅት፣ ከዓለም መሪዎች ውስጥ በዕድሜ ትልቁ፣ የ90 ዓመቱ የካሜሩን ፕሬዚዳንት ፖል ቢያ ናቸው፡፡

በዩናይትድ ስቴትስም፣ በቀጣዩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመወዳደር ከቀረቡት ግንባር ቀደም ዕጩ ተፎካካሪዎች ውስጥ ሁለቱ፣ የዕድሜ ባለጸጎች ናቸው፡፡

የቪኦኤዋ ከፍተኛ የዋሽንግተን ዘጋቢ ካሮሊን ፕሬሱቲ፥ “የዓለም መሪዎች እና ዕድሜያቸው” በሚል ርእስ ያጠናቀረችውን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG