የፋኖ ታጣቂዎች፣ ወሰን ጥሰው፣ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አብቹ እና ኘዓ ወረዳ፣ ዳግም ጥቃት ፈጽመዋል፤ ሲሉ፣ አንድ የወረዳው ባለሥልጣን ገለጹ፡፡
ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት፣ ባለፈው ዐርብ እንደኾነ የገለጹት፣ የወረዳው የኮምዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሓላፊ፣ የመከላከያ ሠራዊት ወደ ወረዳው ከገባ በኋላ እንደወጡ ተናግረዋል፡፡
በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውና የፋኖ ታጣቂ እንደኾነ የገለጸ አንድ ግለሰብ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው ምላሽ፣ የግጭቱ መንሥኤ፥ የኦሮሚያ የጸጥታ ኀይሎች እንደኾኑ ገልጾ፣ ፋኖ፥ ወሰን ጥሶ ገብቶ ጥቃት ፈጽሟል፤ መባሉን አስተባብሏል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም