በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጣልያን ወደ አገሯ በሚጎርፉ ፍልስተኞች እየታገለች ነው


ፋይል - አንድ ወጣት ስደተኛ ሲሲሊ በሚገኘው ካልታጂሮኔ ከተማ በሚገኘው የስደተኞች ጣቢያ ፎቶግራፍ ሲነሳ ይታያል - ሚያዚያ 20፣ 2016
ፋይል - አንድ ወጣት ስደተኛ ሲሲሊ በሚገኘው ካልታጂሮኔ ከተማ በሚገኘው የስደተኞች ጣቢያ ፎቶግራፍ ሲነሳ ይታያል - ሚያዚያ 20፣ 2016

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የጣልያን ደቡባዊ ግዛት በሆነችው ላምፔዱሳ ደሴት ከ4ሺ200 በላይ ፍልስተኞች መድረሳቸውን የአካባቢው ፖሊስ አዛዥ ኢማኑኤል ሪሲፋሪ ለሮይተርስ ተናገሩ፡፡

ጣልያን ከሰሜን አፍሪካ እና የባልካን ሀገሮች የሚመጡ ስደተኞችን ለማስተናገድ እየታገለች ሲሆን የሀገሪቱ ቀይ መስቀል የፍልስተኞችን ቀውስ አስመልክቶ ተጨማሪ ዓለም አቀፍ ጥረቶች እንዲደረጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከስሎቬንያ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘው የጣሊያኗ ትራይሴቴ ከተማ ከንቲባ ሮቤርቶ ዲፒያዛ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በየቀኑ እየጨመረ ስለመጣው የፍልስተኞች ቁጥር ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል፡፡

“እ.አ.አ ከ1990ዎቹ ጀምሮ ከስደተኞች ጋር የተያያዙ ችግሮች ላይ ስሰራ ቆይቻለሁ፣ እንዲህ ያለውን ግን አይቼ አላውቅም” ያሉት ከንቲባው “ከተማዋ አስቸኳይ አደጋ ላይ ናት” ብለዋል፡፡

ጣሊያን በዚህ ዓመት ብቻ ከ107ሺ,500 በላይ የባህር ስደተኞችን ያስተናገደች ሲሆን፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ53 ሺህ ብልጫ ማሳየቱ ተመልክቷል፡፡

የጣሊያን ቀይ መስቀል ፕሬዚዳንት ሮዛሪዮ ቫልስትሮ ጣልያን ብቻ ሳይሆን መላው አውሮፓ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለቀውሱ ውጤታማ ምላሽ በመሰጠት ለቀውሱ እጅ እንዳይሰጡ አሳስበዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG