በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒዠር የፈረንሣይ አምባሳደር ያሉበት አልታወቀም


ፋይል - በስተቀኝ የሚታዩት በኒዠር የፈንሳይ አምባሳደር ሲልቫይን ኢቴ፣ በኒሜይ ለፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ኦሊቪዬ ዱቦይስ ሰላምታ ሲሰጡ - መጋቢት 20፣ 2023
ፋይል - በስተቀኝ የሚታዩት በኒዠር የፈንሳይ አምባሳደር ሲልቫይን ኢቴ፣ በኒሜይ ለፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ኦሊቪዬ ዱቦይስ ሰላምታ ሲሰጡ - መጋቢት 20፣ 2023

በአዲሶቹ የኒዠር መሪዎች ሀገር ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት የፈረንሣይ አምባሳደር ዛሬ ሰኞ ሀገር ለቀው ስለ መውጣታቸው ግልጽ አለመሆኑ ተነገረ፡፡

ባላፈው ዓርብ የኒዠር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አምባሳደር ሲልቫን ኢቴ አገር ለቀው ለመውጣት ያላቸው ጊዜ 48 ሰዓታት መሆኑን አስታውቆ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ትዕዛዙ የተሰጠው፣ አምባሳደር ኢቴ ፕሬዚዳንት መሃመድ ባዙምን ከሥልጣን ካስወገዱ ወታደራዊ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ተገልጿል፡፡

ባዙምና ባቤተሰቦቻቸው በፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት መታሠራቸው ተነግሯል፡፡

ኒዠር የቀድሞ ፈረንሣይ ቅኝ ግዛት ስትሆን ፈረንሣይ እስካሁን በአገሪቱ የተሰማሩ 1ሺ500 ወታደሮች አሏት፡፡

ወታደሮቹ ኒዠር የጅሃድ ኃይሎችን እንድትዋጋ የረዷት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ባላፈው እሁድ በሺዎች የሚቆጠሩ የኒዠር ዜጎች በአገሪቱ ዋና ከተማ ኒያሜ ጎዳናዎች ላይ በመውጣት ባዙምን ላስወገዱት ወታደራዊ መሪዎች ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል፡፡

ፈረንሣይ ለአዲሶቹ የኒዠር መሪዎች ዕውቅና ያልሰጠች ሲሆን በኒዠር ብቸኛው ህጋዊ ባለሥልጣን የባዙም መንግሥት ሆኖ ይቆያል ብላለች፡፡

ባዙም ወደ ሥልጣናቸው እንዲመለሱ ከጠየቀው የምዕራብ አፍሪካው የኢኮኖሚ ህብረት ኢኮዋስ ጋርም ፈረንሣይ እንደምትስማማ አስታውቃለች፡፡

ኢኮዋስ ባዙምን ወደነበሩበት ለመመለስ ወታደራዊ ኃይል እንደሚጠቀም መዛቱ ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG