ፍልስተኞችን አሳፍረው ከቱርክ የባህር ዳርቻ ወደ ግሪክ ደሴቶች ሲያመሩ የነበሩ ሁለት ጀልባዎች በመስጠማቸው በውስጡ የነበሩ አራት ህጻናትን ጨምሮ 5 ፍልስተኞች መሞታቸው ተገለጸ።
የግሪክ ባለሥልጣናት እንደተናገሩት በግሪክ ደሴት ሌስቦስ አቅራቢያ መስጠማቸው በተገመተው ጀልባዎች ውስጥ የነበሩ ሌሎች 18 ፍልስተኞችን ማዳን ተችሏል፡፡
የመንግሥት ቃል አቀባይ ፓቭሎስ ማሪናኪስ በአደጋው የ8 ዓመት ታዳጊ ወንድ ህጻን፣ የ14 እና የስምንት ዓመት እንዲሁም የ11 ወር ህጻን ሴት ልጅ መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡
ዛሬ ሰኞ ማለዳው ላይ ከሳሞስ የኤጂያን ደሴት ወጣ ብሎ የባህር ጠረፍ ጠባቂ ጀልባ 37 ሰዎችን ያሳፈረ ጀልባ መመልከቱን ተገልጿል፡፡
ባለሥልጣናቱ እንደተናገሩት የነፍስ አድን ሥራው የተጀመረው ይህን የጥበቃ ጀልባ የተመለከቱ ፍልስተኞች ወደ ውሃው ውስጥ እየዘለሉ መግባታቸው ከታወቀ በኋላ ነው፡፡
በአደጋው አንዲት ሴት ፍልስተኛ ስትሞት፣ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች በሳምንቱ መጨረሻ በምስራቅ ኤጂያን ደሴቶች በርካቶችን ማዳናቸው ተነግሯል፡፡
ባላፉት ወራት ውስጥ ወደ አካባቢው የሚመጡ የአዳዲስ ፍልስተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱም ተመልክቷል፡፡
መድረክ / ፎረም