በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍሎሪዳ ውስጥ አንድ ነጭ ታጣቂ በሩምታ ተኩስ 3 ጥቁሮችን ገደለ


ፍሎሪዳ ውስጥ አንድ ነጭ ታጣቂ በሩምታ ተኩስ 3 ጥቁሮችን ገደለ
ፍሎሪዳ ውስጥ አንድ ነጭ ታጣቂ በሩምታ ተኩስ 3 ጥቁሮችን ገደለ

አንድ ነጭ ታጣቂ ፣ ፍሎሪዳ -ጃክሰንቪል ከተማ ውስጥ ጥቁሮች በብዛት በሚኖሩበት ሰፈር በሚገኝ ዶላር ጀነራል የተባለ ሱቅ ውስጥ ሶስት ሰዎችን በጥይት ተኩሶ መግደሉ ተሰምቷል። በትናንትናው ዕለት የደረሰውን ጥቃት የአካባቢው የፖሊሳ ሹም “ዘርን መሰረት ያደረገ” እንደሆነ ተናግረዋል ።ጥቃት አድራሹ ራሱን እንዳጠፋም ተገልጿል።

በተጠራ የጋዜጠኞች ማስገንዘቢያ ላይ "(ጥቃት አድራሹ)ጥቁር ህዝቦችን ይጠላል" ሲሉ ቲ.ኬ. ዋተርስ የተባሉት የፖሊስ ሹም ተናግረዋል ።ታጣቂው የግዙፍ ቡድን አባል ስለ መሆኑ ግን ምንም አይነት ማስረጃ እንደሌለ አክለዋል ።

ዋተርስ እንዳሉት ጥቃት አድራሹ በ20ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የነበረ ሲሆን ለጥቃቱ የግሎክ የእጅ ሽጉጥ እና ኤአር-15 ከፊል አውቶማቲክ ጠመንጃ ተጠቅሟል። አንደኛው መሳሪያ ስዋስቲካ ቅርጽ የታተመበት እንደሆነም ተገልጿል።

ራሱን ያጠፋው ጥቃት አድራሽ ከተወው የጽሁፍ መልዕክት በመነሳት፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ፣ ሌላ ጥቃት በቪዲዮ ጨዋታ ውድድር ላይ የእሩምታ ተኩስ በመክፈት ሁለት ሰዎችን ከገደለ በኃላ ራሱን ያጠፋበት 5ኛ ዓመት ከመሆኑ ጋር ተያያዥ እንደሆነ እንዲያምኑ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል ።

አዘጋጆች ነጭ ባልሆኑ ህዝቦች ላይ እየተባባሰ የመጣን የጥላቻ ጥቃት ዙሪያ ትኩረት ለመሳብ ፣ በሀገሪቱ ዋና ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ያካሄዱት የመታሰቢያ ጉዞ በተጠናቀቀ በሰዓታት ውስጥ ነው የአሁኑ ጥቃት የተሰማው ። ዘገባው የአሶሼትድ ፕረስ ነው ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG