በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፊፋ የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትን ለ90 ቀናት አገደ


የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሉዊስ ሩቢያለስ
የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሉዊስ ሩቢያለስ

የፊፋ የዲሲፕሊን ኮሚቴ፣ የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሉዊስ ሩቢያለስ፣ በሴቶች የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ተጫዋቿን መሳም ጨምሮ፣ ያሳዩትን ባህሪ መርምሮ እስኪጨርስ ለ90 ቀናት ከስራ አግዷቸዋል።


ሩቢያለስ የስፔን የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ተጫዋችን ያለፈቃዷ ስመዋል በሚል ስራቸውን በፍቃዳቸው እንዲለቁ ከስፔን መንግስት፣ ከሴት ተጫዋቾች፣ የእግር ኳስ ክለቦች እና ሌሎች ባለስልጣናት ግፊት ቢደረግባቸውም፣ ከኃላፊነታቸው እንደማይነሱ አርብ እለት የስፔን እግር ኳስ ፌደሬሽን ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።


ፊፋ የዲሲፕሊን ኮሚቴው ውሳኔ የሚሰጥበትን የጊዜ ሰሌዳ አላስቀመጠም።

የዲሲፕሊን ዳኞቹ ከማጠንቀቂያ እና ከቅጣት አንስቶ ከስፖርቱ እስከመታገድ የሚደርስ ቅጣት ሊያስተላልፉ ይችላሉ።

ፊፋ አሁን ያሳለፈው ጊዜያዊ እገዳ ሩቢያለስ በእግር ኳስ ዙሪያ ስራቸውን እንዳይሰሩ እና ከሌሎች ባለስልጣናት ያር ግንኙነት እንዳይኖራቸው ሊያግዳቸው ይችላል።


ፊፋ ባወጣው መግለጫ፣ የዲሲፕሊን ኮሚቴው ዳኛ ሆርሄ ፓላሲዮ የተጫዋቿን ሄርሞሶን "መሰረታዊ መብቶች" እና የዲሲፕሊኑን ምርመራ ሂደት ትክክለኛንት ለመጠበቅ ቅዳሜ እለት ጣልቃ መግባታቸውን አመልክቶ፣ ሪቢያሌስ "በራሳቸው ወይም በሶስተኛ ወገን በኩል የስፔን ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የሆነችውን ጄነፈር ሄርሞሶን ወይም በቅርቧ ያሉ ሰዎችን ለማነጋገር ከመሞከር እንዲቆጠቡ" አዘዋል ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG