በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ የደረሰው የኤሌክትሪክ መቋረጥ 12 ሰዓት አስቆጠረ


በኬንያ በተቋረጠው የመብራት አገልግሎት ምክንያት አንዲት ኬንያዊት ኩራዝ አብርታ ተቀምጣ - ነሐሴ 26፣ 2023
በኬንያ በተቋረጠው የመብራት አገልግሎት ምክንያት አንዲት ኬንያዊት ኩራዝ አብርታ ተቀምጣ - ነሐሴ 26፣ 2023

ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ አርብ ዕለት ማታ በኬንያ የደረሰው የኤሌክትሪክ መቋረጥ ቅዳሜ እለትም ቀጥሎ 12 ሰዓት ማስቆጠሩ ተገለፀ።

የመብራት አገልግሎት መቋረጡ የሀገሪቱ ዋና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲዘጋ ያደረገ ሲሆን ዋና ዋና ሆስፒታሎች እና የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ግቢ ጭምር የኤሌክትሪክ መስመር ተቋርጦባቸዋል። አንድ የመንግስት ሚኒስትርም ባልተለመደ መልኩ ህዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቁ አስገድዷል።


የመብራት መቋረጡን ተከትሎ መንግስት አብላጫ የባለቤትነት ድርሻ ያለው የኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ "የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ላይ የደረሰው ችግር በተወሰነው የሀገሪቱ ክፍል ከፍተኛ የኃይል መቋረጥ ማድረሱን" አስታውቋል።

ከለሊቱ ዘጠኛ ሰዓት ጀምሮ ግን በዋና ከተማው ናይሮቢ በሚገኘው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እና አንዳንድ ወሳኝ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መመለሱን መስሪያቤቱ አመልክቷል።

በናይሮቢ የሚገኙ ሶስት ትልልቅ ሆስፒታሎች እና የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጽ/ቤት የሚገኝበት የመንግስት መስሪያቤትን ጨምሮ ግን፣ ሌሎች በርካታ ቦታዎች አሁንም ጀነሬተር እየተጠቀሙ መሆናቸውን ለአሶስዬትድ ፕሬስ ገልፀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG