በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡዳፔስት የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያ ወርቅ እና ብር አገኘች


በቡዳፔስት የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያ ወርቅ እና ብር አገኘች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:00 0:00

በቡዳፔስት የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያ ወርቅ እና ብር አገኘች

በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ነሐሴ 20 በተካሄደው የሴቶች የማራቶን ውድድር፣ ኢትዮጵያ ወርቅ እና ብር ሜዳሊያዎች አግኝታለች።

ውድድሩን 2:24:23 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሯ ያስገኘችው አማኔ በሪሶ ስትሆን፣ "በጣም ተደስቻለው! ለሃገሬ ወርቅ ስላመጣው ተደስቻለው" ስትል ስሜቷል ለአሜሪካ ድምፅ ገልፃለች።

ባለፈው ዓመት በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት የተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች ማራቶን ውድድር ሻምፕዮን የነበረችው ጎይተቶም ገብረስላሴ እንዲሁ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች። ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 5ኛ ደረጃን ይዛ ውድድሩን አጠናቃለች።

ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ፀሀይ ገመቹ በውድድሩ ላይ ለታየው የቡድን ስራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገች ቢሆንም፣ ከ35ኛ ኪሎሜትር በኃላ በተሰማት ከፍተኛ ህመም ምክንያት ውድድሩን ለማቋረጥ ተገዳለች።

በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን ኤቢሳ ነገሰ አትሌቶቹን እና አሰልጣኞቹን አነጋግሮ የላከውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG