ቀሪዎቹ ውድድሮች፣ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይቀጥላሉ፡፡ ሻምፒዮናው፣ በሴቶች እና በወንዶች ማራቶን፣ በወንዶች እና በሴቶች የ5000 ሜትር፣ እንዲሁም በሴቶች የ3000 ሜትር መሰናክል ውድድሮች እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።
ዘጋቢያችን ኤቢሳ ነገሰ፣ በቡዳፔስት የአትሌቶች የልምምድ ጣቢያ ተገኝቶ፣ የ3000 መሰናክል ውድድር ተሳታፊ አትሌቶችንና አሠልጣኞችን አነጋግሯል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።