በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ሰብአዊ ባለሥልጣን የሱዳን ግጭት እየተስፋፋ መሆኑን አስጠነቀቁ


በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን በሱዳን ከሶስት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ የውሃ እና የመብራት በፈረቃ ሲያገኙ የቆዩ ሲሆን፣ አሁንም በስራ ላይ ያሉ የጤና ተቋማት ጋርም መድረስ አልቻሉም።
በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን በሱዳን ከሶስት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ የውሃ እና የመብራት በፈረቃ ሲያገኙ የቆዩ ሲሆን፣ አሁንም በስራ ላይ ያሉ የጤና ተቋማት ጋርም መድረስ አልቻሉም።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ፣ በሱዳን ያለው ግጭት ከቁጥጥር ውጪ መውጣቱን እና ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ በመላ ሀገሪቱ ህልውና ላይ አደጋ መደቀኑን ተናገሩ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ማርቲን ግሪፍትስ ከሚያዝያ አጋማሽ ጀምሮ በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በዋና ከተማዪቱ ጁባ፣ ካርቱም እና ዳርፉር ላይ የሚካሄዱት ከፍተኛ ጦርነት ያደረሰው ውድመት ወደ ደቡብ ምስራቅ ኮርዶፋን ግዛት ተስፋፍቷል ብለዋል።

የመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የሰብአዊነት ባለስልጣን እንደተናገሩት በግጭቶች እና ዝግ በሆኑ መንገዶች ምክንያት በደቡብ ኮርዶፋን ዋና ከተማ ካዱጊሊ የምግብ ክምችት ሙሉ በሙሉ የተሟጠጠ ሲሆን፣ የእርዳታ ሠራተኞችም ለተራቡ ሰዎች እንዳይደርሱ መከልከላቸውን ተናግረዋል ።

በምዕራብ ኮርዶፋን ዋና ከተማ ኤል ፉላ የሰብአዊ ርዳታ ቢሮዎችና የአቅርቦት ቁሳቁሶችም ተዘርፈዋል ብለዋል፡፡

ግጭቱ ለሱዳን የዳቦ ቅርጫት ወደሆነው አካባቢ እየተቃረበ በመምጣቱ በአልጀዚራ ግዛት የሰላማዊ ዜጎች ደህንነት ስጋት እንዳሳደረባቸው ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

"ጦርነቱ በቀጠለ ቁጥር ውጤቱ የከፋ ይሆናል" ያሉት ግሪፍትስ “አንዳንድ ቦታዎች ምግብ አልቆባቸዋል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጋልጠዋል፣ ህክምና ካልተደረገላቸው ለሞት አደጋ ተቃርበዋል፤›› ሲሉ ያለውን የከፋ ሁኔታ አመላክተዋል።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ “ለዚህ ቀውስ የሚገባውን አስቸኳይ ምላሽ ይስጥ” ሲሉ ግሪፍትስ ጠይቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG