የእንግሊዝን ቡድን ያሸነፈው የስፔይን የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ተጫዋችን ያለፈቃዷ ስመዋል የተባሉት የስፔይን እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ከኃላፊነታቸው እንደማይነሱ አስታወቁ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህን ያስታወቁት ከዓለም የሴቶች እግር ኳስ ጨዋታ ፍጻሜ በኋላ ደስታቸውን በሚገልጹበት ወቅት ተጫዋችዋን ያለ ፈቃዷ ከንፈሯ ላይ በመሳማቸው በተሰማው ቁጣ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የቀረበላቸው ግፊት ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ነው፡፡
የፌዴረሽኑ ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቤለስ ማድሪድ ውስጥ በአስቸኳይ ለተሰበሰበው የሬዴሬሽኑ ምክር ቤት “ከሥልጣኔ መልቀቅ አልፈልግም” ማለታቸውን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ሩቤለስ ጂን ሄርሞሶ የተባለቸውን ተጫዋች ከንፈሯ ላይ የሳሙት አውስትራሊያ ውስጥ በተደረገው የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ በነበረው የሽልማት ስነሥርዓት ወቅት መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ድርጊቱ ያስተከተለውን ቁጣ ተከትሎ በርካታ የስፔይን ዜና ማሰራጫዎች ሩቤለስ በገዛ ፈቃዳቸው ከሥልጣን ለመውረድ ማቀዳቸውን ሲዘግቡ ቆይተዋል፡፡
ሩቤለስ ግን ድርጊቱ በሄርሞሶ ፈቃድ “በስምምነት የተፈጸመ መሳሳም ነው” ብለዋል፡፡
ሄርሞሶ ከድርጊቱ በኃላ፣ ባላፈው እሁድ ባስተላለፈችው የቪዲዮ መልዕክት፣ ድርጊቱን “አልወደድኩትም ግን ደግሞ ምን ማድረግ እችላለሁ?” ብላለች።
መድረክ / ፎረም