በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዚምባቡዌያን የምርጫውን ውጤት እየተጠባበቁ ነው


በዚምባብዌ ዋና ከተማ ሃራሬ ጎዳናዎች ላይ፣ ሰዎች የጋዜጣ አርዕስተ ዜናዎችን ሲያነቡ ይታያሉ - ነሐሴ 25፣ 2023
በዚምባብዌ ዋና ከተማ ሃራሬ ጎዳናዎች ላይ፣ ሰዎች የጋዜጣ አርዕስተ ዜናዎችን ሲያነቡ ይታያሉ - ነሐሴ 25፣ 2023

የዚምባቡዌ የጸጥታ ኃይሎች፣ እ.አ.አ በ2018 የተካሄደው ምርጫን ተከትሎ የተቃውሞ ሰልፎችና የሁከት መናኻሪያ ወደ ነበረው ብሄራዊ የምርጫ ማዕከል የሚያመሩ መንገዶችን ዛሬ ዘግተዋል፡፡

ዚምባቡዌያን ደግሞ የምርጫውን ውጤት ዛሬ ዓርብ ለማወቅ በጉጉት እየተጠባበቁ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የዚምባብዌ ምርጫ ኮሚሽን ገዥው ፓርቲ ዛኑ ፒኤፍ 38 የፓርላማ መቀመጫዎችን ሲያሸንፍ ዋና ተቃዋሚው የዜጎች ጥምረት ለለውጥ 32 አሸንፏል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ኮሚሽኑ እስካሁን የተካሄደውን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት እስካሁን ይፋ አላደረገም፡፡

ምርጫው ሐሙስ እለት የተጠናቀቀው፣ በተለይም በአብዛኛው ከተሞች ውስጥ በነበሩ የድምጽ መስጫዎች ላይ ችግር መፈጠሩን ተከትሎ ባለሥልጣናት ምርጫውን በአንድ ቀን እንዲያራዝሙ ከአደረጉ በኋላ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ፖሊስ ባላፈው ረቡዕ በወሰደው ድንገተኛ ርምጃ 41 የምርጫ ተቆጣጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን እና መሳሪያቻቸውንም መያዙን ገልጿል። ተቆጣጣሪዎቹ ኮምፒውተሮቻቸውን እና ሞባይል ስልኮቻቸውን በመጠቀም በህገ-ወጥ መንገድ የምርጫ ድምጽ አሃዞችንና እና የምርጫ ጣቢያዎችን ውጤት ለመከታተል ተጠቅመውበታል ሲልም አመልክቷል።

ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ፣ ዚምባቡዌ የፕሬዝዳንታዊ፣ የህግ አውጭው እና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች ምርጫዎችን ሂደት ሆነ ብላ አላከበረችም ስትል ከሳለች፡፡

በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የ80 አመቱ ኢመርሰን ምናንጋግዋ ለሁለተኛ ጊዜ የስልጣን ዘመን ፈላጊ ሲሆኑ የ የሲ.ሲ.ሲው መሪ 45 ዓመቱ ኔልሰን ቻሚሳ፣ የሀገሪቱን ከፍተኛ የሥልጣን ቦታ ለማግኘት እየተፎካከሯቸው መሆኑ ተነግሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG