በምሥራቅ ሱዳን፣ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሚኖሩበት የኡምራኩባ መጠለያ ጣቢያ፣ በደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ ከ400 በላይ መጠለያዎች እንደፈረሱ፣ ስደተኞች ተናገሩ፡፡ መጠለያቸው ለወደመባቸው ስደተኞችም፣ እስከ አሁን ርዳታ እንዳልተደረገላቸው፣ አስተያየት ሰጪዎቹ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡
የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ሸሽተው፣ ከሦስት ዓመት በፊት፣ ከትግራይ ክልል ወደ ሱዳን የተሻገሩት ስደተኞቹ፣ ቀደም ሲል የነበራቸው የአገልግሎት አቅርቦት በመጓደሉ፣ እየተቸገሩ እንደኾኑ ጠቅሰዋል፡፡ ዓለምአቀፍ ተቋማት፣ በችግራቸው እንዲያግዟቸው ጠይቀው፣ የኢትዮጵያ መንግሥትም፣ ወደ አገራቸው እንዲመልሳቸው፣ አሁንም ለሦስተኛ ጊዜ ተማፅነዋል፡፡
(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ)
መድረክ / ፎረም