በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የሸማቾች ጥበቃ ሕጎች ባለመተግበራቸው ማኅበረሰቡ ለከፍተኛ እንግልት እንደተዳረገ ተሟጋች ድርጅቱ ገለጸ


በኢትዮጵያ የሸማቾች ጥበቃ ሕጎች ባለመተግበራቸው ማኅበረሰቡ ለከፍተኛ እንግልት እንደተዳረገ ተሟጋች ድርጅቱ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:18 0:00

በኢትዮጵያ የሸማቾች ጥበቃ ሕጎች ባለመተግበራቸው ማኅበረሰቡ ለከፍተኛ እንግልት እንደተዳረገ ተሟጋች ድርጅቱ ገለጸ

የሸቀጦች እና የአገልግሎቶች የዋጋ ንረት የመጨረሻው ጫና የሚያርፈው በሸማቹ ላይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ እየተባባሰ ከመጣው የኑሮ ውድነት ጋራ፣ የሸማቹ ማኅበረሰብ መብት እንዳልተከበረና በዚኽም ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረገ እንዳለ፣ የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ዋና ዲሬክተር አቶ ቁምላቸው አበበ ይናገራሉ፡፡

በአንጻሩ፣ የሸማቾችን መብት ለማስጠበቅ ያለሙ በርካታ ዐዋጆች እና ሕጎች እንደወጡ፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት(የግብይት ሥራ አመራር) ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ጌቴ አንዱዓለም ያወሳሉ፡፡ ይኹን እንጂ፣ ዐዋጆቹ እና ሕጎቹ፣ በሥራ ላይ ውለው በተጨባጭ ችግር ሲፈቱ እንዳልታዩ ዶር. ጌቴ ይገልጻሉ፡፡

በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የፀረ ንግድ ውድድር እና የሕግ ጥሰት መከላከል ዴስክ ሓላፊ አቶ ጌትነት አሸናፊ በበኩላቸው፣ መንግሥት፣ የኑሮ ውድነትን ለመከላከል፣ በዓመቱ ውስጥ ከሰባት ቢሊየን ብር በላይ መድቦ፣ ምርት ለኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲደርስ አድርጓል፤ ይላሉ፡፡ የሸማቾችን መብት ለማስጠበቅም፣ ልዩ ልዩ ሕጋዊ ርምጃዎችን እንደወሰደ በማውሳት፣ በመንግሥት ላይ የሚቀርበውን ወቀሳ ተከላክለዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG