በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በተኩስ ልውውጥ በሰነበቱ የዐማራ ክልል አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም መኖሩ ተገለጸ


በተኩስ ልውውጥ በሰነበቱ የዐማራ ክልል አካባቢዎች ዛሬ አንጻራዊ ሰላም መኖሩ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:12 0:00

በተኩስ ልውውጥ በሰነበቱ የዐማራ ክልል አካባቢዎች ዛሬ አንጻራዊ ሰላም መኖሩ ተገለጸ

በዐማራ ክልል፣ ሰሞኑን፣ አለመረጋጋት እና የተኩስ ልውውጥ የነበረባቸው የጎንደር እና ሸዋሮቢት ከተሞች፣ ዛሬ አንጻራዊ ሰላም እንደሚታይባቸው፣ አስተያየት ሰጭዎች ተናገሩ፡፡

በባሕር ዳር ከተማ፣ ዛሬ ረፋድ ላይ ውጥረት የነበረ ቢኾንም፣ ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ፣ ከተማዋ በመደበኛ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ነዋሪዎች ጠቁመዋል፡፡

ይኹን እንጅ፣ መንግሥታዊ መዋቅሩ የማይንቀሳቀስባቸው፣ በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ እና መካነ ሰላም ከተሞች፣ የማዘጋጃቤት እና ሌሎች አገልግሎቶች እንደተስጓጎሉ መኾናቸውን፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን አንጾኪያ ገምዛ ወረዳ መኮይ ከተማ አካባቢ፣ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር፣ የአሜሪካ ድምፅ የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ፣ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የክልሉን ዞኖች ከባሕር ዳር ከተማ፣ እንዲሁም ከዐዲስ አበባ ከተማ ጋራ የሚያገናኙና ተዘግተው የነበሩ ዋና ዋና መንገዶች እና መሥመሮች ተከፍተዋል፤ ብሏል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG