በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ራማፎሳ የዓለም ኢኮኖሚዎች አፍሪካ ላላት አቅም እውቅና እንዲሰጡ ጥሪ አቀረቡ


በጆሃንስበርግ እየተካሄደ ያለው የብሪክስ ጉባዔ
በጆሃንስበርግ እየተካሄደ ያለው የብሪክስ ጉባዔ

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ ብሪክስ በሚል የእንግሊዘኛ ምኅጻር የሚታወቀው የአምስት አገሮች ስብስብ መስፋፋት ጋር ተያይዞ፣ የዓለም ኢኮኖሚ ተዋናይ የሆኑት ሀገራት አፍሪካ ያላትን አቅም እንዲቀበሉ በመጠየቅ የደቡብ አፍሪካን አቋም በድጋሚ አሳውቀዋል።

ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን ያቀፈው የብሪክስ ቡድን በዓለም ላይ ትልቁ የታዳጊ ኢኮኖሚ ስብስብ ሲሆን፣ እነዚህ በማደግ ላይ ያሉ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ያላቸውን ትስስር ማሻሻል በሚችሉበት መንግድ ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

"የአፍሪካ ሀገራት ምርጫቸው፣ ወደ አህጉራችን መጥተው መዋዕለ ነዋይ የሚያፈሱ ብቻ ሳይሆኑ ጥሬ ሀብቱን እዚሁ ምንጩ ባለበት የሚጠቀሙ መሆኑን ግልፅ አድርገዋል" ያሉት ራማፎሳ "ምክንያቱም የአፍሪካ ሀገራት ፍላጎታችን ድንጋይ እና አሸዋ ወደ ውጪ መላክ ብቻ ሳይሆን፣ ያለቁ ምርቶችን መላክ መቻል ነው" ሲሉ አስታውቀዋል።

ከአምስቱ የብሪክስ አባል ሀገራት የተውጣጡ፣ ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ የሚበልጡ ተወካዮች እና ከሌሎች ታዳጊ ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች የሚገኙበት የብሪክስ ጉባዔ በደቡብ አፍሪካ ትልቁ ከተማ ጆሃንስበርግ እየተካሄደ ሲሆን በአካል ያልተገኙት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሞስኮ የስብስቡን ሊቀመንበርነቷን ተጠቅማ ቡድኑ በዓለም ላይ ያለውን ሚና እንደምታጠናክር፣ እንዲሁም በመጪው ዓመት ጥቅምት የሚደረገውን ጉባዔ በካርዛን እንደምታስተናግድ ገልፀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG