በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጀርመን የዜግነት ህግ ለማላላት ተስማማች


ፋይል - በጀርመን የሚገኙ ስደተኞች
ፋይል - በጀርመን የሚገኙ ስደተኞች

የጀርመን ካቢኔ፣ ስደተኞች ዜግነት ለማግኘት የሚፈጅባቸውን ጊዜ ለማሳጠር እና ጥምር ዜግነት ለመያዝ የሚፈቀድላቸውን ሰዎች ቁጥር ለመጨመር የቀረበውን እቅድ ረቡዕ እለት አፅድቋል።

ገና በፓርላማ በሚጸድቀው አዲሱ ህግ መሰረት በጀርመን ዜግነት ማግኘት የሚቻልበት ጊዜ ከስምንት ዓመት ዝቅ ብሎ አምስት አመት እንዲሆን ተደርጓል። ከማህበረሰቡ ጋር በቀላሉ መዋሃድ የቻሉ እና ጥሩ የጀርመን ቋንቋ ችሎታ ያላቸው ደግሞ ከሶስት ዓመት በኃላ ዜግነት ማግኘት ይችላሉ።

የጀርመን ዜግነት የሚያገኙ ሰዎች በመንግስት ላይ ጥገኛ አለመሆናቸውን ማሳየትም ይጠበቅባቸዋል።

አዲሱ የዜግነት ረቂቅ ህግ በጀርመን የሚኖሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቱርክ ማህበረሰቦችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ጥምር ዜግነት መያዝ እንዲችሉም በር ይከፍታል።

እስካሁን ድረስ ጥምር ዜግነት የመያዝ መብት፣ ለአውሮፓ ህብረት እና ስዊዘርላንድ ዜጎች ብቻ የተገደበ ሆኖ ቆይቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG