በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ፍርድቤት ሜታ እና ያባረራቸው ሰራተኞቹ ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱ 21 ቀን ሰጠ


ፋይል - የፌስቡክ አርማ የያዘ ዘመናዊ ስልክ ከእናት ካምፓኒው ሜታ አርማ ጋር አብሮ ይታያል።
ፋይል - የፌስቡክ አርማ የያዘ ዘመናዊ ስልክ ከእናት ካምፓኒው ሜታ አርማ ጋር አብሮ ይታያል።

የኬንያ ፍርድቤት፣ የፌስቡክ እናት ካምፓኒ የሆነው ሜታ እና፣ ያለአግባብ ከስራ በመባረር ክስ የመሰረቱበት የይዘት ተቆጣጣሪ ሰራተኞቹ፣ አለመግባባታቸውን ከፍርድቤት ውጪ እንዲፈቱ 21 ቀን መስጠቱን፣ ረቡዕ እለት የወጣው የፍርድቤት ትዕዛዝ አመለከተ።

184 ይዘት ተቆጣጣሪዎች ሜታ እና ሌሎች ሁለት የስራ ተቋራጮቹን የከሰሱት፣ የሰራተኞች ማህበር በመመስረታቸው 'ሳማ' ከተሰኘው አንደኛው የስራ ተቋራጭ ድርጅት በመባረራቸው መሆኑን አስታውቀዋል። ፌስቡክ የስራ ተቋራጩን ከቀየረ በኃላ፣ ለክሰምበርግ በሚገኘው እና 'ማጆሬል' በተሰኘው ሁለተኛው ስራ ተቋራጭ ድርጅት ውስጥም በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ እንዳይቀጠሩ ስማቸው በጥቁር መዝገብ ላይ እንዲሰፍር መደረጉንም ከሳሾቹ አመክተዋል።

ክሱን የተመለከተው የቅጥር እና ሰራተኛ ግንኙነት ፍርድቤት ባሳለፈው ውሳኔ "ከሳሾቹ አቤቱታቸውን ከፍርድቤት ውጪ በሽምግልና እንዲፈቱ" ያለ ሲሆን፣ የከሳሽ ጠበቆች እንዲሁም የተከሳሾቹ ሜታ፣ ሳማ እና ማጆሬል ጠበቆች ፈርመውበታል።

ሁለቱም ወገኖች ችግራቸውን በ21 ቀናት ውስጥ መፍታት ካልቻሉ ጉዳያቸው በፍርድቤት መታየት እንደሚቀጥልም ውሳኔው አመልክቷል።

ሜታ፣ ሳማ እና ማጆሬል በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ምላሽ አልሰጡም። ሆኖም በሚያዚያ ወር አንድ ዳኛ፣ ሜታ በምስራቅ አፍካዊቷ ሀገር ውስጥ በይፋ ተመዝግቦ ባይንቀሳቀስም ኬንያ ውስጥ ተቀጥረው በሚሰሩት የይዘት ተቆጣጣሪዎች ግን ሊከሰስ እንደሚችል ውሳኔ አሳልፈው ነበር።

የክሱ ሂደት ሜታ በቀጣይ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ የይዘት ተቆጣጣሪዎቹ ጋር በሚኖረው የስራ ግንኙነት ላይ አንድምታ እንደሚኖረው ተመልክቷል።

ቀደም ሲልም የሜታ የቀድሞ የይዘት ተቆጣጣሪ ሴማ ውስጥ ባለ መጥፎ የስራ ሁኔታ ዙሪያ ኬንያ ውስጥ ክስ መስርቶ ነበር። ሁለት ኢትዮጵያውያን ጥናት አጥኚዎች እና አንድ የመብት ተቋምም ፌስቡክ ከኢትዮጵያ የሚወጡ የሁከት እና የጥላቻ ፅሁፎች እንዲስፋፉ አድርጓል በሚል ክስ የመሰረቱበት ሲሆን ሁለቱም ክሶች በሂደት ላይ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG