በየዓመቱ፣ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍሎች በድምቀት የሚከበረውና ሻደይ፥ አሸንዳ፥ አሸንድዬ፥ ሶለል በሚሉ ልዩ ልዩ ስያሜዎች የሚታወቀው ክብረ በዓል፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት ምክንያት፣ በትግራይ ክልል ሳይከበር አራት ዓመታትን አሳልፏል።
ይኹንና፣ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ዘንድሮ፣ የልጃገረዶች ጨዋታ በዓል የኾነው አሸንዳ፣ በትግራይ ክልል በአደባባይ እየተከበረ ነው።
በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ፍጻሜን ተከትሎ መከበር የሚጀምረው በዓሉ፣ “የሰላም ተስፋ ያየንበት ነው፤” ብለዋል ተሳታፊዎች።
ሙሉጌታ አጽብሓ
መድረክ / ፎረም