በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አለበል አማረ ተይዘው ያሉበትን እንደማያውቁ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ


ባህር ዳር ከተማ
ባህር ዳር ከተማ

ቀድሞ በነበረው የአማራ ክልል አደረጃጀት የሰላም ግንባታ እና የደህንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊነት የነበሩት ኮሎኔል አለበል አማረ ባለፈው ሀሙስ ከመሥሪያ ቤታቸው ‘ፀጥታ አስከባሪዎች ናቸው’ በተባሉ ሰዎች ተይዘው መወሰዳቸውንና ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን እስካሁን እንደማያውቁ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ኮሎኔል አለበል ከሚሠሩበት የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የተወሰዱት ከሁለት ጠባቂዎቻቸው ጋር መሆኑን ወንድማቸው አቶ ገበየሁ አማረ መግለፃቸውን ሪፖርተራችን አስቴር ምሥጋናው ከአዲስ አበባ ዘግባለች።

በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች ህዝቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን በክልሉ ሰላም ማስፈን ችሏል

ኮሎኔል አለበል በሰኔ 2011 ዓ.ም. የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራር አባላት ላይ ከተፈፀመው ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ለጥቂት ወራት ታስረው እንደነበር ተገልጿል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ “ባለፉት አሥራ ሦስት ቀናት አከናወንኳቸው” ብሎ ባወጣው የግምገማ ሪፖርት “በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች ህዝቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን በክልሉ ሰላም ማስፈን ችሏል” ሲል ለመንግሥቱ የዜና አገልግሎት ገልጿል፡፡

እዙ ይህንን ይበል እንጂ በክልሉ በምሥራቅና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች አሁንም ውጥረት እንዳለ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቪኦኤ ተግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG