በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰደድ እሳት በስፔን ተኔሪፌ ደሴት ብዙዎችን አፈናቀለ


በስፔን ግዛት ቴኔሪፌ የተከሰተ የዱር ሰደድ ነሐሴ 2015
በስፔን ግዛት ቴኔሪፌ የተከሰተ የዱር ሰደድ ነሐሴ 2015

የስፔን ግዛት በሆነችው ቴኔሪፌ የተከሰተው የዱር ሰደድ እሳት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን መኖሪያ ቀያቸውን ለቀው እንዲሄዱ አስገድዷል። ትላንት ቅዳሜ ማምሻውን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱ በ10 ከተሞች ተዳርሷል ያሉ ሲሆን፤ የ11 ከተማ ነዋሪዎችን ለጥንቃቄ ሲባል አካባቢዎችን እንዲለቁ እየተደረገ ነው ብለዋል።

እስከ ትላንት ማምሻ ድረስም ስምንት ሺ ሄክታር በ70 ኪሜ የሚሆን አካባቢ መጎዳቱ ቢገለጽም ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ እሳቱ ዋና ዋና የቱሪዝም መዳረሻ የሚባሉት ጋር አልደረሰም ተብሏል። የአካባቢው ባለስልጣናት እስካሁን በቀጠለው ጥረት ከ26000 ዜጎች ውስጥ 12 ሺ የሚደርሱ ዜጎች አካባቢውን እንዲለቁ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል።

ከፍተኛ ሙቀት እና ደረቅ የአየር ጸባይ በአውሮፓ ደኖች ላይ የሰደድ እሳት እንዲከሰት እያደረገ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ሳይንቲስቶች እየገለጹ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG