በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኒጀር ሁንታዎች የሲቪል አስተዳደር ይመሰረታል አሉ


የኒጀሩ ሁንታ ጄኔራል አቦድራህማኔ ትቼኒ 2015
የኒጀሩ ሁንታ ጄኔራል አቦድራህማኔ ትቼኒ 2015

በኒጀር በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ፕሬዘዳንትን የገለበጡት ወታደራዊ ሁንታዎች ሀገሪቱን በቀጣይ 3 ዓመታት ወደ ሲቪል አመራር ትመለሳለች ሲሉ ትላንት ቅዳሜ ማምሻውን ገለጹ።

ጄኔራል አቦድራህማኔ ትቼኒ በዕቅዱ ላይ ምንም ዓይነት ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። ይሁን እንጂ በቀጣይ 30 ቀናት ውስጥ የሽግግሩ መመሪያዎች በሁንታው በሚዘጋጅ ውይይት አማካኝነት ይወሰናሉ ሲሉ በሀገሪቱ ብሔራዊ ጣቢያ ላይ ተናግረዋል።

ጄነራሉ “ከቀውሱ ለመውጣት በጋራ ልንሰራባቸው በምንችላቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ይኖረናል የሚለው አሳምኞኛል” በማለት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራትን ቀውስ ለማቆም ካለመው ልዑክ ጋር በተወያዩበት ወቅት ተናግረዋል።

በናይጄሪያው የቀድሞ ፕሬዘዳንት ጄኔራል አብዱሳላሚ አቡባክር የሚመራው የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብር የኤኮዋስ ተወካዮች ቡድን በተናጥል ከስልጣን የወረዱትን የኒጀር ፕሬዘዳንት ሞሃመድ ባዙምን ጎብኝተዋል። ጉብኝቱ በምዕራብ አፍሪካ እና በሳህል ቀጠና የመንግስታቱ ድርጅት ልዩ ተወካይ ሊኦናርዶ ሳንቶስ ሲማኦ አርብ ዕለት ወደ ኒጀር ከመድረሳቸው ጋር የተቀናጀ ጥረት ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG