በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዘጠኝ ሺሕ በላይ ፈታኝ መምህራንና የፈተና አስፈጻሚዎች ወደየአካባቢያቸው ተመለሱ


ከዘጠኝ ሺሕ በላይ ፈታኝ መምህራንና የፈተና አስፈጻሚዎች ወደየአካባቢያቸው ተመለሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00

ከዘጠኝ ሺሕ በላይ ፈታኝ መምህራንና የፈተና አስፈጻሚዎች ወደየአካባቢያቸው ተመለሱ

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት፣ በዐማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡትን ኹሉንም መምህራን፣ ወደየአካባቢያቸው እንደመለሰ፣ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ስለ ጉዳዩ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት፣ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዲሬክተር ዶር. እሸቱ ከበደ፣ በዐማራ ክልል የተመደቡትና ከክልሉም ወደ ሌሎች ክልሎች የተመደቡት፣ በድምሩ ከዘጠኝ ሺሕ በላይ ፈታኝ መምህራንና የፈተና አስፈጻሚዎች ኹሉም ወደየአካባቢያቸው እንደተመለሱ ተናግረዋል፡፡

ፈታኝ መምህራኑንና የፈተና አስፈጻሚዎቹን፣ በቻርተርድ አውሮፕላንና በመኪና ማስወጣት እንደተቻለም፣ ዋና ዲሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ፈታኝ መምህራንም፣ ከዐማራ ክልል በሰላም እንደወጡና ከቤተሰቦቻቸው ጋራ እንደተቀላቀሉ ተናግረዋል፡፡ የጅማ ዩኒቨርሲቲም እንዲሁ፣ በዐማራ ክልል ተመድበው የነበሩ መምህራኑ ኹሉም፣ በሰላም እንደተመለሱ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG