ብራዚል፥ ሩሲያ፥ ሕንድ፥ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን ያቀፈው በእንግሊዝኛው ምኅጻር “ብሪክስ” ቡድን ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ፣ በመጪው ማክሰኞ፣ በጆሃንስበርግ ይከፈታል።
እስከ ኀሙስ በሚዘልቀው በዚኹ ጉባኤ፣ ከሚቀርቡት ዋና ዋና አጀንዳዎች መካከል፣ ዐዲስ አባል ሀገራትን በመጨመር፣ የቡድኑን ጂኦፖለቲካዊ ኀይል የማስፋት ጉዳይ፣ ዋናው እንደሚኾን ይጠበቃል።
የቪኦኤዋ ኬት ባርትሌት፣ ከዝግጅቱ አንሥቶ በውዝግብ በታጀበው ጉባኤ፣ ምን ዐይነት ውይይት እንደሚጠበቅ፣ ተንታኞችን አነጋግራ ያጠናቀረችውን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም