በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሪክስ አባል ሃገሮች መሪዎች ደቡብ አፍሪካ ይሰበሰባሉ


10ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ሳንድተን፣ እአአ ሐምሌ 24/ 2018
10ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ሳንድተን፣ እአአ ሐምሌ 24/ 2018

ከዓለም ምጣኔኃብት ሩቡን ድርሻ በያዙ አምስት ሃገሮች የተመሠረተው የብሪክስ ቡድን መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንደሚሰበሰቡ ተገለፀ።

መሪዎቹ በዚህ ስብሰባቸው ላይ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተፈጠረውን ቡድን ወደ ጂዖ-ፖለቲካ ኃይልነት በመቀየር ‘የምዕራባውያኑን ተፅዕኖ ለመገዳደር ያስችለናል’ የሚሉትን መላ ሳያበጁ እንደማይቀር ይሰማል።

በስብሰባው ላይ ከመሥራች አባል ሃገሮቹ የብራዚል፣ የህንድ፣ የቻይናና የደቡብ አፍሪካ መሪዎች በአካል እንደሚሳተፉና የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን ግን እንደማይገኙ ታውቋል።

ፑቲን ዩክሬን ውስጥ የጦር ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በተገኙበት እጃቸው እንዲያዝ ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ከጥቂት ወራት በፊት ማዘዣ ማውጣቱ ይታወሳል።

ስብሰባው በተጨማሪም እያደገ ከመጣው ቡድኑን የመቀላቀል ጥያቄ አንፃር በተለይ የአፍሪካ ሃገሮችን በማቀፍ ለመስፋፋት በሚችልበት ሁኔታ ላይም ይወያያል ተብሏል።

ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ በይፋ ካስገቡ ሃገሮች መካከል ነች።

ቡድኑ “በዕርዳታና በንግድ አፍሪካን ለማማለል አቅዷል” ሲል ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

የዓለም አካሄድ ‘ለአሜሪካና ለባለጠጋ አጋሮቿ ፍላጎት ያደላ ነው’ የሚለው ቅሬታ “ለብሪክስ መፈጠር ዋና ምክንያት ነው” ሲል ዘገባው አክሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG