እየተገባደደ ባለው 2015 ዓ.ም.፣ ፍቺ የሚፈጽሙ የዐዲስ አበባ ከተማ ባለትዳሮች ቁጥር፣ ካለፈው ዓመት ጋራ ሲነጻጸር በእጥፍ እንደ በለጠ፣ የዋና ከተማዋ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል።
የኤጀንሲው የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ዲሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሤ፣ በዚኽ ዓመት፣ ፍቺ ለመፈጸም ወደ መሥሪያ ቤታቸው የመጡት ባለትዳሮች ቁጥር ከፍተኛ እንደኾነ ተናግረዋል።
የጋብቻ እና የቤተሰብ አማካሪ የኾኑት አቶ ይመስገን ሞላ፣ ትዳራቸውን ለማትረፍ ምክር ፈልገው የሚመጡ ቤተሰቦች ብዛት፣ በየጊዜው እየጨመረ እንደመጣ ገልጸውልናል።
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም