በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ኢትዮጵያ የዐዲሶቹ ክልሎች የመንግሥት ሠራተኞች ምደባ ብርቱ የኢ-ፍትሐዊነት ቅሬታ ቀረበበት


በደቡብ ኢትዮጵያ የዐዲሶቹ ክልሎች የመንግሥት ሠራተኞች ምደባ ብርቱ የኢ-ፍትሐዊነት ቅሬታ ቀረበበት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:14 0:00

በደቡብ ኢትዮጵያ የዐዲሶቹ ክልሎች የመንግሥት ሠራተኞች ምደባ ብርቱ የኢ-ፍትሐዊነት ቅሬታ ቀረበበት

የቀድሞ የደቡብ ክልል መንግሥት ሠራተኞች፣ በዐዲሶቹ ክልሎች የተደረገው ምደባ፣ “ኢፍትሐዊ እና ከፍላጎታችን ውጭ ነው፤” ሲሉ፣ ቅሬታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።

በቁጥር የበዙ ሠራተኞች፣ ትላንት እና ዛሬ፣ የቅሬታ ዶሴያቸውን ይዘው፣ ወደ ክልሉ ርእሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የተመሙ ሲኾን፣ “በደል ደርሶብናል፤” ሲሉ አማርረዋል።

የክልሎቹ ማደራጃ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት እና የደቡብ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ፣ በአወዛጋቢው የሠራተኞቹ ምደባ ጉዳይ፣ ማብራርያ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልኾኑ፣ በተለያየ መንገድ ገልጸዋል።

የክልሉ መንግሥት ተጠሪ እና በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ ባለፈው ሳምንት፣ ሠራተኞች ለማኅበራዊ ቀውስ ሳይጋለጡ፣ በዐዲሶቹ ክልሎች እንዲመደቡ፣ የተጠና ስልት እንደተዘጋጀ ተናግረው ነበር።

ይኹንና ሠራተኞቹ፣ ምደባው “ኢ-ፍትሐዊ እና ማኅበራዊ መሠረቶቻችንን ያናጋ ነው፤” ሲሉ፣ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG