በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እውን ኢትዮጵያ ለሐቀኛ የሽግግር ፍትሕ ዝግጁ ናት?


አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፣ አቶ ያሬድ ስዩም፣ አቶ አዲ ቄቄቦ፣ አቶ ደመቀ መኮንን፣ አልባብ ተስፋዬ
አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፣ አቶ ያሬድ ስዩም፣ አቶ አዲ ቄቄቦ፣ አቶ ደመቀ መኮንን፣ አልባብ ተስፋዬ

የፕሪቶርያውን በዘላቂነት ተኩስ የማቆም የሰላም ስምምነት ተከትሎ፣ ከኢትዮጵያ አኳያ ባሕርይው፣ የአፈጻጸም ስልቱ እና የውጤት ማኅቀፉ ለተወጠነው የሽግግር ፍትሕ፥ አማራጭ የፖሊሲ ሐሳቦች የሚያቀርብ የባለሞያዎች ቡድን፣ በፍትሕ ሚኒስቴር ሥር እንዲቋቋም ተደርጎ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡

አሁን ላይ፣ የሽግግር ፍትሕ፣ በርግጥም ለኢትዮጵያ ቢያስፈልጋትም፣ ከጅምሩ የመንግሥት ሚና የአንበሳውን ድርሻ መያዙ ግን፣ በገለልተኛነቱ እና ተኣማኒነቱ ላይ ጥያቄ እንደሚያሥነሳ፣ የሕግ ባለሞያዎች፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

እውን ኢትዮጵያ ለሐቀኛ የሽግግር ፍትሕ ዝግጁ ናት?
please wait

No media source currently available

0:00 0:23:22 0:00

በቀጣይም፣ አደረጃጀቱን ከፍትሕ ሚኒስቴር ውጭ በገለልተኛ ኮሚሽን እንዲዋቀር ማድረግ ካልተቻለ፣ በሽግግር ፍትሕ የመንግሥት አካላት ተጠያቂነት የማይታለፍ ኾኖ ቢገኝ፣ ትግበራውን አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ባለሙያዎቹ ያመለክታሉ፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG