በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጣልቃ ገብነት በበዛበት የአፍሪቃ ቀንድ ተለዋዋጭ ፖለቲካ የቀጣናው ሀገራት በጋራ ሊሠሩ እንደሚገባ ምሁራን አሳሰቡ


ዶ/ር ሳሙኤል ተፈራ፣ አቶ አብዱራሃማን ሳይድ
ዶ/ር ሳሙኤል ተፈራ፣ አቶ አብዱራሃማን ሳይድ
የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባሕር አካባቢ፣ ከመልክአ ምድራዊ ዘርፈ ብዙ ፋይዳው አኳያ፣ የተለያዩ ዓለማዊ ኀይሎች ፍላጎቶች እና ጥቅሞች መስሕብ እና መናኸሪያ እንደኾነ ይታወቃል፡፡
የቀንዱ ሀገራት እና ቀጣናዊ ተቋማትም፣ እጅግ ተለዋዋጭ የኾነውን የእነኚኽን ሉላዊ ኀይሎች ፍላጎቶች እና ጥቅሞች ታሳቢ በማድረግ፣ የሕዝቦቻቸውን ጥቅም ለማረጋገጥ፣ በጋራ መሥራት ባለባቸው ወቅት ላይ እንደሚገኙ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ምሁራን ያስገነዝባሉ፡፡
በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና እስያ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ፣ ልዕለ ኀያላን ሀገራትን ጨምሮ፣ ልዩ ልዩ ጥቅሞች ያላቸው አካላት፣ ከመቸውም ጊዜ በተለየ፣በቀይ ባሕር አካባቢ ላይ አተኩረው እየተሰባሰቡ እንዳሉ ይገልጻሉ፡፡ከዚኽም ጋራ በተያያዘ፣ በቀንዱ ሀገራት የውስጥ ፖለቲካ ላይ፣ የበዙ ጣልቃ ገብነቶች እየታዩ እንደኾነ፣ ዶር. ሳሙኤል ይናገራሉ፡፡

የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካን በቅርበት የሚከታተሉት፣ ኤርትራዊው የፖለቲካ ተንታኝ አብዱራሃማን ሰይድ በበኩላቸው፣ በዓለም ፖለቲካዊ ሥርዐት ላይ እየታዩ ያሉ ለውጦች፣ የቀይ ባሕር አካባቢን ተፈላጊነት እየጨመረው ስለ መምጣቱ ያመለክታሉ፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG