በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዋጋ ንረትን ለመቀነስ የታቀደባቸው የብሔራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ቁጥጥር ማሻሻያዎች የተግባራዊነት እና የጊዜ ፈተና

የዋጋ ንረትን ለመቀነስ የታቀደባቸው የብሔራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ቁጥጥር ማሻሻያዎች የተግባራዊነት እና የጊዜ ፈተና
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:14 0:00

የዋጋ ንረትን ለመቀነስ የታቀደባቸው የብሔራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ቁጥጥር ማሻሻያዎች የተግባራዊነት እና የጊዜ ፈተና

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በአገሪቱ እየተባባሰ የመጣውን የዋጋ ንረት ለመቀነስ ያስችላሉ፤ ያላቸውን የፖሊሲ ርምጃዎች፣ ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ፣ ነሐሴ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሀገር ውስጥ የመንግሥት ብዙኀን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ የታቀዱት የገንዘብ እና የፊሲካል ፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ በ2016 ዓ.ም. የዋጋ ንረቱን፣ ወደ 20 በመቶ እና በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ከ10 በመቶ በታች ለማውረድ ያለመ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ምሁር፣ ዶክተር ሰውአለ አባተ፣ ውሳኔዎቹን በተግባር ማዋል ከተቻለ፣ ውጤት ያመጣሉ፤ ብለው ያምናሉ።

የኢኮኖሚ እና ቢዝነስ ጉዳዮች አማካሪው ዶክተር ተፈሪ ዳባ በበኩላቸው፣ ምርታቸውን ወደ ውጭ የሚልኩ አምራቾችን ለማበረታት የተላለፉ ውሳኔዎች፣ በአጭር ጊዜ ውጤት ማምጣት የሚችሉ አይደሉም፤ ይላሉ፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG