በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኒዤሩ ሁንታ የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ለመክሰስ ማቀዱ ‘በጣም አሳሳቢ ነው’ ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪክ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪክ

የኒዠሩ ወታደራዊ ሁንታ መሪዎች በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትንና በኃይል ከስልጣን ያስወገዷቸውን፣ ፕሬዝዳንት መሀመድ ባዙምን በከፍተኛ የሃገር ክህደት ወንጀል ለመከሰስ የያዙት ሙከራ “በጣም አሳሳቢ ነው” ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪክ ተናገሩ።

ወታደራዊ ሁንታው ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ጉዳዩን በተመለከተ ዋና ጸሃፊው ያላቸውን አቋም እና በአንጻሩም የመንግስታቱ ድርጅት የሚወስደው ተጨባጭ እርምጃ ስለመኖሩ በጋዜጠኞች የተጠየቁት ዱጃሪክ ሲመልሱ፡ “የፕሬዚዳንቱ እና የቤተሰባቸው ጤና እና ደህንነት በጣም ያሳስበናል። አሁንም ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እና ወደ ኃላፊነታቸው እንዲመለሱ እንጠይቃለን” ብለዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም፣ በፖለቲካው ረገድ የምዕራብ አፍሪቃው ልዩ ተወካይ ሊዮናርዶ ሳንቶስ ሲማኦ አቡጃ እንደሚገኙና፣ ከምዕራብ አፍሪቃው የምጣኔ ሃብት ማሕበረሰብ (ኢኮዋስ) እና ከአፍሪቃ ሕብረት ጋር ግንባር ፈጥረው በትብብር በመስራት ላይ በመሆናቸው “ሁኔታውን ለመቀልበስ” ያሳደረባቸውን ተስፋ አመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG