በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ በተፈጸመ ጥቃት 26 ሰዎች እንደተገደሉ ተገለጸ


በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ በተፈጸመ ጥቃት 26 ሰዎች እንደተገደሉ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:19 0:00

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ በተፈጸመ ጥቃት 26 ሰዎች እንደተገደሉ ተገለጸ

በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ አደባባይ፣ ኤፍኤስአር በተባለ ተሽከርካሪ ተጭነው በነበሩ ወጣቶች ላይ፣ ትላንት እሑድ በተፈጸመ የከባድ መሣሪያ ጥቃት፣ 26 ሰዎች እንደሞቱ እና 50 የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል እንደገቡ፣ የፍኖተ ሰላም ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ፍንዳታው በከተማው ሲከሠት፣ በዐይን ግምት ከ10 እስከ 15 ሜትር ርቀት ላይ እንደነበረ የተናገረ አንድ እማኝ፣ በከተማው አደባባይ ላይ በግምት ሁለት ሺሕ የሚደርስ ሕዝብ እንደነበርና ከእነርሱም ከፊሉ ኤፍኤስአር በተባለ መኪና ላይ እየተሰቀሉ እንደነበር ገልጿል፡፡

በድንገት ከባድ የፍንዳታ ድምፅ እንደተሰማ፣ ለደቂቃዎች ራሱን ስቶ እንደነበርና ከደቂቃዎች በኋላ ሲነቃ፣ ቁጥሩ የበዛ ሰው ሞቶ እና ቆስሎ እንደተመለከተ፣ የዐይን እማኙ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ በዐማራ ክልል በደብረ ብርሃን፣ በፍኖተ ሰላም እና በቡሬ ከተሞች፣ በከባድ መሣሪያ ተኩስ በተፈጸመ ድብደባ፣ ዐያሌ ሰላማዊ ሰዎች እንደተጎዱ፣ የመኖሪያ አካባቢዎች እና ሕዝባዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም እንደወደሙ፣ ደረሱኝ ያላቸውን ተኣማኒ ሪፖርቶች በመጥቀስ አመልክቷል።

ስለ ጥቃቱ እና ደረሰ ስለተባለው ጉዳት፣ ከመንግሥት በኩል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶር. ለገሰ ቱሉ የእጅ ስልክ ላይ ደጋግመን ብንሞክርም፣ ጥሪው ባለመነሣቱ ምላሽ ለማግኘት አልቻልንም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG