የአፍሪካ ኅብረት በኒጄር ቀውስ ላይ ለመነጋገር ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ስብሰባ ተቀምጧል። “የአፍሪካ ኅብረት የሠላም እና የጸጥታ ም/ቤት በኒጄር ስላለው ወቅታዊ ሁኔታና እና ችግሩን ለመፍታት እየተደረገ ስላለው ጥረት ማብራሪያ ያደምጣል” ሲል ኅብረቱ ቀድሞ ትዊተር፣ አሁን X ተብሎ በሚጠራው ማኅበራዊ መድረክ አስታውቋል።
በስብሰባው ላይ ከሚሳተፉት ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት እና የኒጄር ተወካዮች ይገኙበታል። በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተነሱትን ሞሃመድ ባዙምን አስመልክቶ ሙሳ ፋኪ ማሃማት ባለፈው ሳምንት ሲናገሩ፣ አያያዛቸው “ተቀባይነት የሌለው ነው” በማለት ሁኔታው “እጅግ አሳስቦኛል” ብለዋል።
ወታደራዊ ሁንታው ትናንት እሁድ በምርጫ ስልጣን የያዙትን ሞሃመድ ባዙምን “በሀገር ክህደት” እንደሚከስ አስታውቆ፣ የቀጠናውን የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኤኮዋስ) በኒጄር ላይ የጣለውን ማእቀብ አውግዟል።
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም