በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ወደ ኒጀር ወታደሮችን ለመላክ መሰናዳታቸውን ተከትሎ ውጥረት ተባብሷልየምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ወደ ኒጀር ወታደሮችን ለመላክ መሰናዳታቸውን ተከትሎ ውጥረት ተባብሷል
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ወደ ኒጀር ወታደሮችን ለመላክ መሰናዳታቸውን ተከትሎ ውጥረት ተባብሷል

በኒጀር አዲስ ወታደራዊ አገዛዝ እና ኒጀርን ወደ ዲሞክራሲን ለመመለስ ወታደሮችን ለማስፈር ትዕዛዝ ባስተላለፈው የምዕራብ አፍሪካ ቀጠና ማህበረሰብ መካከል ውጥረቱ እየተባባሰ ነው።

ኢኮዋስ በሚል ምሕጻረ መጠሪያ የሚታወቀው የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ከስልጣን የተባረሩትን ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ባዙም ወደ ስልጠናቸው እንዲመለሱ ያስቀመጠው ቀነ -ገደብ ባለፈው እሁድ ካለቀ በኋላ፣ በኒጀር ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ያለመ “ተጠባባቂ ኃይል” ለማሰማራት መወሰኑን ሐሙስ ዕለት አስታወቋል።

ከሰዓታት በፊት ሁለት የምዕራባውያን ሀገራት ባለስልጣናት ለአሶሼትድ ፕሬስ
እንደተናገሩት የኒጀር ወታደራዊ አገዛዝ ሀገራት የቀደመውን አስተዳደር ለመመለስ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት የሚሞክሩ ከሆነ ፕሬዚደንት ባዙምን እንደሚገድሉ ለከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት አስታውቀዋል።


የኢኮዋስ ኃይል መቼ እና የት እንደሚሰማራ ብሎም ዛቻው 15 አባል ሀገራት ባሉት ማህበረሰብ ውሳኔ ላይ ምን ዓይነት ውጤት እንደሚኖረው እስካሁን ግልፅ አይደለም ። የግጭት አጥኞች ይሰማራል የተባለው ኃይል በናይጄሪያ የሚመራ 5,000 ያህል ወታደሮችን እንደሚይዝ እና በሳምንታት ውስጥ ዝግጁ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል ።

ከኢኮዋስ ስብሰባ በኋላ የጎረቤት ሀገር አይቮሪኮስት ፕሬዝዳንት አላሳን ኦውታራ ሀገራቸው ከናይጄሪያ እና ቤኒን ጋር በወታደራዊ ዘመቻ እንደምትሳተፍ ተናግረዋል።

ኦውታራ በመንግስቱ ቴሌቪዥን ላይ አንድ አይቮሪ ኮስት አንድ የፋይናንስ ዝግጅቶቹ የተጠናቀቀለት ባታሊዮን ጦር እንደምታዘምት ተናግረዋል ።

25 ሚሊዮን የሚጠጉ ህዝቦች ያሏት ድሃይቱ ሀገር ኒጀር፣ ከአልቃይዳ እና ከኢስላሚክ መንግስት ቡድን ጋር ግኑኝነት ያላቸውን ጂሃዲስት አማጽያን ለመመከት የምዕራባውያን አጋር ሀገራት የመጨረሻ ተስፋዎች አንዷ ሆና ቆይታለች ። ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ስቴትስ በኒጀር ከ2,500 በላይ ወታደራዊ ሰራተኞች አሏቸው ። ሀገራቱ ከሌሎች የአውሮፓ አጋሮች ጋር በመሆን የኒጀርን ወታደራዊ ኃይል ለማጠናከር በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አፍስሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG