በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዐማራ ክልል ዋና ዋና ከተሞች ሰላማዊ ድባብ ሰፍኖባቸው እንደዋሉ ነዋሪዎች ተናገሩ


የዐማራ ክልል ዋና ዋና ከተሞች ሰላማዊ ድባብ ሰፍኖባቸው እንደዋሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:39 0:00

የዐማራ ክልል ዋና መዲና - ባሕር ዳር፣ መጠነኛ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መኖሩንና የአየር ትራንስፖርትም እንደተጀመረ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡

ኾኖም፣ ሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ በሚጠቀስ ደረጃ እንዳልተከፈቱ የገለጹ አስተያየት ሰጪዎች፣ በጸጥታ አካላት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየተፈጸመ እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

በጎንደር እና በሸዋሮቢት ከተሞችም፣ ሰላማዊ ድባብ ማስተዋላቸውን፣ አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል፡፡ ይኹንና፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንደተዘጉ መኾናቸው፣ ለኅብረተሰቡ ስጋት እንዳሳደረበት ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ይህንኑ፣ የኅብረተሰቡን ቅሬታ አስመልክቶ፣ ከመንግሥት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በርካታ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ አካላት፣ በዐማራ ክልል ያለው ግጭት እንዳሳሰባቸው እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ደግሞ፣ “በዐማራ ክልል ያለው ግጭት፣ በመተማ እና በክልሉ ሌሎችም አካባቢዎች፣ ሰብአዊ ርዳታ እንዳይሰጥ አድርጓል፤” ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG