ለጋሾች፣ ለሱዳኑ ሰብአዊ ቀውስ፣ የ1ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ርዳታ ሰጥተዋል። ግጭቶች ባሉባቸው የተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱት የረድኤት ቡድኖች እንደሚሉት፣ ለርዳታ የሚውል ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት መኖሩ፣ ብርቱ ፈተና ደቅኗል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ግጭቱን እየሸሹ ከሱዳን ወደ ጎረቤት ሀገራት የተሰደዱ ወገኖች በበኩላቸው፣ በሔዱባቸው ሥፍራዎች ያገኙት ሰብአዊ ምላሽ፣ እጅግ ደካማ በመኾኑ፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ መገደዳቸውን ይናገራሉ። ሄንሪ ዊልኪንስ ከሬንክ ደቡብ ሱዳን ባጠናቀረው ዘገባ፣ ርዳታው ያጠጠበትን መንሥኤ ይመረምራል።