በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፍሎሪዳ የተሸጠ ሎተሪ የ1ነጥብ58 ቢሊዮን ዶላር አሸናፊ ኾነ


የኤሌክትሮኒክስ ቢልቦርድ ኒውዮርክ ከተማ
የኤሌክትሮኒክስ ቢልቦርድ ኒውዮርክ ከተማ

ነዋሪነታቸው በዩናይትድ ስቴትስ ፍሎሪዳ ግዛት የኾነ አንድ የሎተሪ ተጫዋች ግለሰብ፣ 1ነጥብ58 ቢሊዮን ዶላር አሸነፉ።

ባለዕድሉ ግለሰብ፣ ከፍተኛውን የገንዘብ ሽልማት ያገኙት፣ ሜጋ ሚሊዮን ሎተሪ ተጫውተው ሲኾን፣ ባለ10 አኀዙ ሽልማት፣ ከቀደምቶቹ ከፍተኛው እንደኾነ፣ የሎተሪ አወዳዳሪው ትላንት ማክሰኞ አስታውቋል።

የሜጋ ሚሊዮን የገንዘብ ሽልማት አሸናፊው፣ ከሚያዝያ ወር ወዲህ ይፋ የተደረጉ የመጀመሪያው ግለሰብ ናቸው።

የሽልማት መጠኑ ከተረጋገጠ፣ በአሜሪካ የሎተሪ ታሪክ፣ ሦስተኛው ትልቁ ሽልማት እንደሚኾን፣ ኤቢሲ የተሰኘው የአሜሪካ ቴሌቭዥን ጣቢያ ዘግቧል።

የሎተሪው አሸናፊ መገኘቱን ተከትሎ፣ ሜጋ ሚሊዮን ባወጣው መግለጫ፣ “ያለምንም ዕድል 31 ዕጣዎች ከወጡ በኋላ፣ አሸናፊውን ዕጣ የያዙት የፍሎሪዳ ግዛቱ ባለዕድል፣ በሜጋ ጃክፖት ጨዋታ ትልቁ ሽልማት የኾነውንና በአሁኑ ሰዓት 1ነጥብ58 ቢሊዮን ዶላር እንደኾነ የተገመተውን ሽልማት አግኝተዋል፤” ብሏል።

ከዚኽ ቀደም ከፍተኛ የነበረው፣ እ.አ.አ በ2018 የተሰጠው 1ነጥብ537 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር፣ የሎተሪ አወዳዳሪው አስታውሷል።

እስከ አሁን ማንነታቸው በይፋ ያልተገለጸው አሸናፊ፣ 783 ሚሊዮን ዶላሩን፣ በአንድ ጊዜ በጥሬ ገንዘብ መውሰድ የሚችሉ ሲኾን፣ ሙሉ ሽልማቱን መውሰድ ከመረጡ ደግሞ፣ በ30 ዓመት ክፍያ የሚያልቅና በየዓመቱ አምስት ከመቶ የሚጨምር ክፍያ በየዓመቱ መውሰድ ይችላሉ።

አብዛኞቹ የሎተሪ አሸናፊዎች፣ የአንድ ጊዜ ክፍያን ሲመርጡ፣ ኸሉም አሸናፊዎች የገቢ ግብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG