በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ የፖለቲካ ተቀናቃኞች ከተቃውሞ በኋላ አዲስ ንግግር ጀመሩ


የመንግሥትን ግብር ጭማሪ በመቃወም ፀረ-መንግሥት ተቃውሞዎች፣ ናይሮቢ ኬንያ
የመንግሥትን ግብር ጭማሪ በመቃወም ፀረ-መንግሥት ተቃውሞዎች፣ ናይሮቢ ኬንያ

በኬንያ መንግሥት እና ተቃዋሚዎች ዛሬ ረቡዕ አዲስ ንግግር ጀምረዋል፡፡ በከረረ የፖለቲካ ሽኩቻ ውስጥ የቆዩት ሁለቱ ወገኖች ንግግር ናይሮቢ ላይ የጀመሩት በኑሮ ውድነቱ እና የምርጫ አፈጻጸም ማሻሻያ እንዲደረገ በመጠየቅ በተከታታይ ሲካሄድ የቆየውን ሁከት የቀላቀለ ተቃውሞ ተከትሎ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱም ወገኖች ቀውሱን ለመፍታት ምንም ዓይነት የሥልጣን ክፍፍል እንደማይኖር አጥብቀው ተናግረዋል።

አንጋፋው ተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ከመጋቢት ወር ጀምሮ በፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ መንግስሥት ላይ ለ10 ቀናት የሚቆይ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ማደራጀታቸው ሲታወስ በተወሰኑት ላይ በተቃዋሚዎች በፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ፍጥጫ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፡፡ መንግሥታዊ መረጃዎች በግጭቱ ቢያንስ 20 ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ የመብት ተሟጋቾች በበኩላቸው የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከዚያ እንደሚበልጥ ተናግረዋል፡፡

ድርደር ከሩቶ የኬንያ ኩዋንዛ ጥምረት ጋር ምንም ዓይነት የሥልጣን ክፍፍል አናደርግም ወይም አንዳችም  የግል ጥቅም ከህዝብ ጥቅም  አናስቀድምም"

በክፍለ አህጉሩ ከሁሉም የተረጋጋ ዴሞክራሲ ባላት በኬንያ የተነሳው ሁከት በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ድንጋጤ ሲፈጥር ፍጥጫውን የሚያቆም ሽምግልና እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።

የኦዲንጋ ልዑካን ቡድን መሪ ካሎንዞ ሙሶካ "እዚህ የተሰበሰብንባቸው ጉዳዮች ውይይት፣ ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልፅግና የፓርቲ ጉዳዮች አይደሉም። እነዚህ የኬንያ ጉዳዮች ናቸው" በማለት ተናግረዋል፡፡

አክለውም "ድርደር ከሩቶ የኬንያ ኩዋንዛ ጥምረት ጋር ምንም ዓይነት የሥልጣን ክፍፍል አናደርግም ወይም አንዳችም የግል ጥቅም ከህዝብ ጥቅም አናስቀድምም" ብለዋል፡፡

የሩቶ ፓርቲ ተወካይ በበኩላቸው ፓርቲያቸው የኬኒያውያንን ጥቅም እንደሚያስቀድም አመልክተው ውይይቱ ፍሬያማ እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG