ባለፈው ሳምንት፣ በማዕከላዊ ሜዲትሬኒያን ባሕር በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ፣ 41 ፍልሰተኞች፣ ሰጥመው እንደሞቱ፣ የአንሳ ዜና አገልግሎት፣ ዛሬ ረቡዕ ዘግቧል፡፡
ዜና አገልግሎቱ፣ በሕይወት ተርፈው ላምፔዱሳ ደሴት የደረሱ አራት ሰዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በሰጠመችው መርከብ ላይ፣ ሦስት ሕፃናትን ጨምሮ 45 ሰዎች፣ በጀልባ ላይ ተሳፍረው እንደነበር፣ ለነፍስ አድን ሠራተኞች ተናግረዋል፡፡
ይኸው የአደጋ ዜና፣ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች፥ ባለፈው እሑድ፣ ሁለት ጀልባዎች እንደተገለበጡና 30 ተሳፋሪዎቻቸው እንዳልተገኙ ከተናገሩት ጋራ የተያያዘ ይኹን አይኹን አልታወቀም፡፡
የባሕር ወሰን ጠባቂዎች፣ በሕይወት የተረፉ 57 ሰዎች እና የሁለት ሰዎች አስከሬን እንዳገኙ አስታውቀዋል፡፡ ከሰጠሙት ጀልባዎች ቢያንስ አንደኛው፣ ባለፈው ኀሙስ ከሴፋክስ ዳርቻ የተነሣ እንደነበረ ተዘግቧል፡፡
መድረክ / ፎረም