በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢላን ማስክ እና ማርክ ዙከርበርግ የቡጢ ፍልሚያ ሊያደርጉ ነው


ኢላን ማስክ እና ማርክ ዙከርበርግ
ኢላን ማስክ እና ማርክ ዙከርበርግ

የቴስላ እና የ“X” ባለቤት ኢላን ማስክ ከሜታ (ፌስቡክ) ባለቤትና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ ጋር በማህበራዊ ሚዲያ በቀጥታ የሚተላለፍ የቡጢ ፍልሚያ ሊያደርጉ መሆኑን ዛሬ ተናገሩ፡፡

ማስክ ይህን የተናገሩት ቀድሞ ትዊተር ይባል በነበረውና አሁን "X" ተብሎ በሚጠራው ገጻቸው ላይ ነው፡፡

ጎምቱዎቹ የማህበራዊ ሚዲያ ሰዎች በላስ ቬጋስ በሚደረገው ማርሻል አርት የተቀላቀለበት የቡጢ ፍልሚያ (cage fight) ለማድረግ ካለፈው ሰኔ ጀምሮ ሲሞካከሩ መቆየታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

“የዙክ እና መስክ” ፍልሚያ በ X ላይ በቀጥታ ይተላለፋል፣ ከሱም ጋር ተያይዞ የሚገኘው ገቢ በሙሉ ለአርበኞች በጎ አድርጎት ይውላል” ሲሉ ዛሬ እሁድ ማለዳው ላይ የተናገሩት ማስክ ተጨማሪ ዝርዝር አልሰጡም፡፡

“የፍልሚያው ትርጉሙ ምንድነው?” ተብለው በX ተጠቃሚ የተጠየቁት ማስክ “ ይህ የሰለጠነ የጦርነት ዓይነት ነው፡፡ ወንዶች ጦርነት ይወዳሉ” ሲሉ መልሰዋል፡፡

ማስክ ይፋ ስላደረጉት መረጃ አስተያየት እንዲሰጥ የተጠየቀው ሜታ ምላሽ አለመስጠቱን ሮይተርስ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ የ39 ዓመቱ ዙከርበርግ እና የ51 ዓመቱ ማስክ በየፊናቸው ልምምድ እያደረጉ መሆኑ ዘገባው አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG