በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕ ለቀረቡባቸው ተጨማሪ ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ መለሱ


የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአውሮፓዊያኑ በ2021 ከዋይት ሀውስ ይዘዋቸው ወጥተዋል ከተባሉ ሚስጥራዊ ሰነዶች ጋር በተያያዘ የተነሱባቸውን ሶስት አዳዲስ ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ማለታቸውን የፍርድ ቤት መዝገብ አርብ እለት አሳይቷል።

ለመጪው 2024 የሪፐብሊካን ፕሬዚዳንታዊ እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ትራምፕ የፊታችን የአውሮፓዊያኑ ነሐሴ 10 በተከሰሱባቸው ሶስት ተጨማሪ ክሶች ላይ በፍሎሪዳ ፌደራል ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቢጠየቁም እንደማይቀርቡ አስታወቀዋል።

ውሳኔው ትራምፕ በዚህ ሳምንት በዋሺንግተን ዲሲ የፌደራል ፍ/ቤት በመቀረብ በሌላ ልዩ ክስ የ2020 ምርጫ አልተሸነፍኩም በማለት ለመቀልበስ ሞክረዋል ለሚለው ክስ ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ ምላሽ ከሠጡ በኋላ የተወሰደ ነው።

ትራምፕ ባለፈው ወር በ37 ክሶች የነበሩባቸው ሲሆን በአሁን ሰዓት 40 ክሶች ቀርበውባቸዋል። የሱ ቫሌት ዋልት ናዉታ የተሰኙት የትራምፕ ተላላኪ እና ሌላው የእሳቸው ሰራተኛ ካርሎስ ደ ኦቬራ ላይ አቃቤ ህግ ባለፈው ሳምንት ክስ መስርቶባቸውል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG