በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የዚምባቡዌ ገዢ ፓርቲ ደጋፊዎች የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችን ገደሉ” የዓይን እማኞች


ዚምባቡዌ 2015
ዚምባቡዌ 2015

በዚህ ሳምንት በዚምባብዌ ተቃዋሚ ደጋፊ ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ጥቃት የገዥው ፓርቲ ተከታዮች ተግባር መሆኑን የዓይን እማኞች አርብ ዕለት ተናገሩ። ሁኔታው በዚህ ወር የሚካሄደው ብሄራዊ ምርጫ ላይ በኃይል ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

የተቃዋሚው የዜጎች ጥምረት ለለውጥ ወይም ሲሲሲ የተሰኘው ፓርቲ ሐሙስ ዕለት በዋና ከተማዋ ሃራሬ የጠራው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ እየሄዱ በደረሰ ጥቃት ቲንሼ ጂትሰንግ መሞታቸውን ይፋ አድርጓል። ሲሲኤፍ ገዢው ፓርቲ ዛኑ ፒኤፍን ወንጅሏል።

ትላንት አርብ የዓይን እማኞች ቺትሰንግ በግሌን ቪው ከተማ የዛኑ ፒኤፍ ከኔቴራ የለበሱ ከ10 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሲመታና በድንጋይ ሲወገር ተመልከተናል ሲሉ ለአሶሺየትድ ፕሬስ ተናግረዋል። በጥቃቱ ቢያንሰ 15 ሌሎች ሰዎች ተጎድተዋል ሲሉ እማኞቹ ተናግረዋል።

ፖሊስ ከቺትሰንግ አሟሟት ጋር በተያያዘ 10 ሰዎችን ማሰሩን ገለጾ እገር ግን የግድያውን ዓላማ እና ከዛኑ ፒአኤፍ ጋር በተያያዘ ያሉ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሳይሰጥ ቀርቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG