የትምህርት ሚኒስቴር፣ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ በዩኒቨርሲቲው ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ፣ 16 ሺሕ ተማሪዎች የተወሰኑ ፈተናዎችን እንዳልወሰዱ፣ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።
በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ፣ የምግብ ብክለት እንዳጋጠመና ተማሪዎች ወደ ሕክምና ገብተው እንደነበር የገለጹት ሚኒስትሩ፣ 38 ተማሪዎች ፈተና መውሰድ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።