በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ወቅት ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩና ለሰላማዊ ውይይት ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ ኢሰመኮ አሳሰበ


በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ወቅት ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩና ለሰላማዊ ውይይት ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ ኢሰመኮ አሳሰበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:25 0:00

የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ዛሬ ዐርብ፣ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በአካሔደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ በዐማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ እንዲታወጅ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

ዐዋጁ ለስድስት ወራት እንደሚቆይ የተደነገገ ሲኾን፣ ዐዋጁን ጥሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው እስከ አሥር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ተመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ወቅትም ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩና ለሰላማዊ ውይይት ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ ኢሰመኮ አሳስቧል፡፡

የኢሰመኮ የባሕርዳር ቅርንጫፍ ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፤ በክልሉ ያለው የሰብአዊ ቀውስ አሳሳቢ መኾኑን ጠቅሰው፣ “ግጭቱ በሰላም ካልተፈታ የሰብአዊ ሁኔታው ችግር ይበልጥ ሊባባስ ይችላል” ብለዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ መካከል የተኩስ ልውውጦች እየተካሔዱ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG