ዋይት ሐውስ፣ በኒዤር የተካሔደውን መፈንቅለ መንግሥት፣ በቅርበት እየተከታተለው እንደኾነ አስታወቀ፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲም፣ ሠራተኞቹን ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ለማስወጣት ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪዎች፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትን ፕሬዚዳንት፣ እስከ ፊታችን እሑድ ወደ ሥልጣን እንዲመልሷቸው የጊዜ ገደብ ከሰጣቸው፣ ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኤኮዋስ) ጋራ ተፋጥጠዋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ብቻ ሳትኾን፣ ሞስኮ እና ቤጂንግም፣ የኒዤርን ወቅታዊ ኹኔታ እየተከታተሉና ተጽእኖአቸውን ለማስፋት የሚያስችሉ ዕድሎችንም በመቃኘት ላይ እንደኾኑ፣ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡
የቪኦኤዋ አኒታ ፓወል ከዋሽንግተን ያጠናቀረችው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም