በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በስዊዲን በኤርትራውያን የባህል ፌስቲቫል ላይ ተቃዋሚዎች ቃጠሎ አደረሱ

በስዊዲን ስቶክሆልም በመካሄድ ላይ በሚገኝ የኤርትራውያን የባህል ፌስቲቫል ላይ፣ አንድ ሺህ የሚሆኑ የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎች ገብተው እሳት መለኮሳቸውን ተከትሎ ብጥብጥ እንደተነሳ  የስዊዲን ጋዜጦች ዘግበዋል።

የስዊዲን ፖሊስ የተጎዱ ሰዎችን በተመለከተ ወዲያውኑ ሪፖርት ባያወጣም፣ የሃገሪቱ ጋዜጦች ግን በርካቶች መጎዳታቸውን እና ብጥብጥ እንደነበር ዘግበዋል።

ጋዜጦቹ አክለውም፣ ተቃዋሚዎቹ እሳት መለኮሳቸውን እና ድንኳኖችን ማፈራረሳቸውን እንዲሁም በታዳሚዎቹ ላይ ድንጋይ መወርወራቸውን ዘግበዋል።

በስዊዲን በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን እንደሚኖሩ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG